ንጉሥ አሳና ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ሕግ በታማኝነት ጠብቀው፣ እያንዳንዱን ጣዖት አፍርሰው፣ ሕዝባቸውንና መንግሥቶቻቸውን እግዚአብሔር እስካላቸው ድረስ ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆን በማያወላውል እምነት አስተዳድረዋል። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ለሕዝባቸው ሰላም ሰጣቸው፣ እጅግም የተትረፈረፈ በረከትና ክብር ሰጣቸው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመዘገበው ታሪክ አማካኝነት፣ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በረከቱን የመቀበል መንገድን አሳይቷል። አሳ በኋለኛው ዘመኑ እንዳደረገው ሁሉ እግዚአብሔርን ሳንፈልግ ወደ ኃያላን መንግሥታት እርዳታ የመጠየቅ ኃጢአት መሥራት የለብንም። እንዲሁም ኢዮሣፍጥ እንዳደረገው ክፉ ድርጊት ከሚፈጽሙ ወይም ከጎናቸው ሆነው ማንኛውንም ጥረት ከሚያደርጉ ጋር መተባበር የለብንም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን ስንረሳና በዙሪያችን ባሉ ሰዎችና ሁኔታዎች ላይ ስንታመን፣ እርሱ በረከቱን ከእኛ ስለሚያነሳ ነው።
እነርሱም በአሳ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ ዐምስተኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። በዚያ ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለ እግዚአብሔር ሠዉ። የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔር ን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ። በፍጹም ልባቸው ስለ ማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሠኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው። 2 ዜና መዋዕል 15፥10–15
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት