ሐዋርያው ጳውሎስ የሦስተኛውን ሰማይ ክብር ስለተመለከተ ታላቅ ነብይ ሆነ። የሰው ልጅ ሊገነዘበው በማይችለው ሰፊ አጽናፈ ዓለም ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለእኛ አስደናቂ የወደፊት ጊዜ አዘጋጅቶልናል። ለዚህም ነው ሰፋ ያለ እይታ እንዲኖረን፣ ወደ ምድር ሳይሆን ወደ አጽናፈ ዓለም - ማለትም ወደ መንግሥተ ሰማያት - እንድንመለከት የጠራን።
የዛሬውን ችግሮች በመንግሥተ ሰማያት ክብር እና እዚያ በሚጠብቀን አስደናቂ የወደፊት ጊዜ ላይ በማተኮር ማሸነፍ አለብን። በመንግሥተ ሰማያት ማመን ካልቻልን፣ በጊዜያዊ ሥቃይ ውስጥ እምነታችንን እናጣለን እና እውነትን እንተዋለን። ሆኖም፣ የመንግሥተ ሰማያትን እውነታ በትክክል ከተረዳን፣ እምነታችን በየቀኑ እያደገ ይሄዳል፣ ይህም ከክብሩ እንድንካፈል ያስችለናል።
የሥጋን ነገር ማሰብ ሞት ነው፤ የመንፈስን ነገር ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ሮሜ 8:6
በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ተስፋው የሚታይ ከሆነ ግን ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ነገር ግን ገና ያላየነውን ተስፋ ብናደርግ፣ በትዕግሥት እንጠብቀዋለን። ሮሜ 8:24–25
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት